ህጻንት እንዳይጨነቁ መርዳት

አንዳንድ ጊዜ ታዳጊ ህጻናት መሻሻል ላያሳዩ ይችላሉ።

የህጻን እድገት ሲጨምር ረጋ ማለትና እኛም አብረን መራመድ መቻል አለብን። ብዋሁን ጊዜ ቤተሰብ የሆኑ ብዙ አስጨናቂ ነገሮች ያጋጥማቸዋል።

ለምሳሌ፡ ብዙ ሰዓታት መሥራት፣ ከትዳር መፋታት፣ መታመም፣ ያለሥራ መቀመጥና ቤት በመቀየር ህጻናትንና ጎልማሳ አዋቂዎችን እንደሚጎዳ ነው። አንድ ህጻን ሲወለድ ለቤተሰብ ጥሩ ጊዜ እንደማይሆንና ይህም ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ከፍተኛ ለውጥ ሲሆን በተለይ ለህጻናት ከፍተኛ ለውጥ ይሆናል። በምናሳድግበት ጊዜ እነዚህ ለውጦች ተፅእኖ ይኖራቸዋል። በነዚህ ጊዚያት የሚኖርዎት ስሜት የልጆችዎን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ጠንካራ ምላሽ ለመስጠት ላያስተውሉ ይችሉ ይሆናል።

በልጅነት ጊዜ ምን ይፈጠራል?

ህጻናት የመፍራትና ያለመተማመን ስሜት ሊያድርባቸው ስለሚችል የሆነ ለውጥ ሲመጣና በሚጨነቁበት ጊዜ ለችግር የተጋለጡ ምስሎ ይሰማዎታል።

በልጆዎት ላይ ስለሚፈጠረው ሁኔታ ይረዳዋል ብለው አይገምቱም። ይህ ግራ የሚያጋባና ያልተረጋጉበት ጊዜ ሊሆን ይችላል።

በሚወዱት ሰው ላይ ስለሚደርሱ መጥፎ ነገሮች ህጻናት ሀላፊነት ሊወስዱ ይችላሉ።

ህጻናት በተለያየ መንገድ ለውጥ ወይም ጭንቀት ሲያጋጥማቸው የሚያደርጉት፡

  • ጸባያቸው ወደታች እንድ ህጻን ያደርጋቸዋል። ይህም ለነሱ እንደበዛባቸው ለመግለጽ የሚያሳዩት ዘዴ ሲሆን ለእርስዎ በፈለጉት መንገድ ለማሳወቅ ነው።
  • የርስዎን ክትትል፣ እንክብካቤ፣ ድጋፍና ምክር ለማግኘት ሲሉ ህጻናት የመከታተል፣ የጥያቄ ወይም የመረበሽ መንፈስ ሊያድርባቸው ይችላል።
  • እንቅልፍ ሊያጡ፣ ሊቃዡ ወይም አልጋ ላይ ሊሸኑ ይችላሉ።
  • በቀላሉ ብስጩ ወይም ነገሮችን በቀላሉ ሊያቆሙ ይችላሉ።
  • ለቤተሰብ የሚበጀውን ለመፍጠር ጥረት ሊያደርጉ ይችላሉ።
  • እርስዎን ላለማስጨነቅ ወይም ላለማበሳጨት ሲሉ ስሜታቸውን ለርስዎ መግለጽ ይከብዳቸዋል።

ምን እንደሚደረግ ….

  • ህጻናትን እንደሚወዷቸው ምን ጊዜም ማረጋገጥ ነው።
  • በተፈጠረ ችግር የርሱ ጥፋት እንዳልሆነ መንገር ይሆናል። ይህም በተለያየ ጊዚያት ሊከሰት ይችላል።
  • ምንም እንኳን ቢበሳጩም እርስዎን እንደተቆጣጠሩ ለነሱ ማሳወቅ ነው።
  • በሚከሰቱ ሁኔታዎች ላይ ለህጻናት ታማኝና ግልጽ መሆን አለብዎት።
  • ከተቻለ ህጻናትን በሚመለከት ውሳኔ አሰጣጥ እነሱንም ማካተት ይሆናል።
  • ህጻናትን ለማነጋገር ጊዜ መመደብ ይሆናል። እርስዎን ማነጋገር ካልቻሉ ለሚያምኑት ሌላ ሰው እንዲያነጋግሩ ማበረታታት ይሆናል።
  • ህጻናት የተለያየ ስሜት ሊኖራቸው እንደሚችል ማሳወቅ ነው። ስሜታቸውን ለመግለጽ የሚችሉበትን መንገድ ማሳየትና ምንም ችግር እንዳልሆነ ማረጋገጥ ነው።
  • ስሜታቸው እንዴት እንደሆነ ለመረዳት ጊዜ መውሰድና እንዴት ጸባያቸው እንደዚያ ሊሆን እንደቻለ ማወቅ። ታጋሽና ጽኑ ታታሪ መሆን ያስፈልጋል።
  • በተለመዱ አሠራሮች ላይ ጽኑ ታታሪ ለመሆን መሞከር ነው።

እርስዎንና ህጻናትን ለመርዳት በአካባቢዎ ለሚኖሩ ሰዎች ማረጋገጥ ነው።

Listen
Update Required To play the media you will need to either update your browser to a recent version, enable javascript or update your Flash plugin.