አያቶችና ልጅ ማሳደግ

አያቶች ልጅ በማሳደግና በቤተሠብ ውስጥ ያላቸው ሚና ባለፉት 30 ዓመታት እየተለወጠ መጥቷል። አያቶች ከልጅ ልጅቻቸው ጋር የሚጫወቱት ሚና እንደ ቤተሰቡ ሁኔታ ይለያያል። አያት ለመሆን ምንም አይነት መመሪያ የለም። እያንዳንዱ አያት ድጋፍ በመስጠትና ጣልቃ በመግባት ማለትም እነርሱ ልጆቻቸውን ባሰደጉት መልክ ማሳደግ ወይም ልጆቻቸው በፈለጉት መንገድ ልጆቻቸውን እንዲያሰድጉ በመተው መካከል መጓዛ አለባች።

አንዳንድ አያቶች ከቤተሠባቸው ጋር በመኖር ወላጆች ሥራ በሚሠሩበት ጊዜ ልጆቻቸውን ይጠብቁላቸዋል። እነዚህ አያቶች በልጅ ልጆቻቸው ህይወት ላይ የጎላ ተሳትፎ ያደርጋሉ አንዳንድ ጊዚም የልጅ ልጆቻቸውን በማሳደግ ቤተሠባዊ ሃላፊነት ይወስዳሉ። ከልጅ ልጆቻቸው ጋር የማይኖሩ አያቶችም ልጆቻቸውን በመንከባከብ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ለምሣሌ ልጆቹን ከትምህርት ቤት በመውሰድና ከትምህርት ቤት በማምጣት ፤ከትምህርት ሰዓት በሁዋላ እና ትምሀርት ቤት በእረፍት ሲዘጋ ልጆችን በመንከባከብ አብሮ በማሰለፍ።

በአንዳንድ ቤተሰቦች ውስጥ አያቶች ሰራ በመስራት ላይ ሰለሆኑ ምንአልባት በልጅ ልጆቻቸው ህይወት ውስጥ የጎላ ሚና ለመጫወት አይችሉ ይሆናል ወይም ላይፈልጉ ይችላሉ። እደነዚህ አይነት አያቶች ‘ልጆችን ለመጠበቅ’ ወይንም ትንሽ ሰአት ከልጆ ልጆጃቻቸው ጋር ለማሳለፍ እነርሱና የልጅልጆቻቸው ቤተሰቦች በሚያመቻቸው ጊዜ ከልጅ ልጆቸው ጋር ትንሽ ሰዓት ያሳልፋሉ።

ሌሎቹ አያቶች ደግሞ ከልጅ ልጆቻቸው ጋር በተደጋጋሚ የማይገናኙ ወይም እስከነ አካቴው ምንም ላይገናኙ ይችላሉ። ለዚህም የተለያየ ምክንያት ሊኖር ይችላል ማለትም ከቤተሠቦቻቸው እርቀው በመኖራቸው ወይም ከቤተሠባቸው ጋር ባላቸው ቅራኔ ሊሆን ይችላል። ይህም አያቶች የልጅ ልጆቻቸው ህይወት እድገት ላይ በለመሳተፋቸው ባየተዋር የተደረጉ እየመሠላቸው ለጭንቀት መንስኤ ሊሆን ይችላል።

በአሁን ጊዜ ወላጆች ልጆቻቸውን ማሳደግ ባለመቻለቸው ወይም ወላጆች ላማሰደግ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው አያቶች በራሳቸው ቤት የልጅ ልጆቻቸው ሙሉ በሙሉ አሳዳጊ መሆን እየጨመረ መጥቷል።

ምንጊዜም ቢሆን አያቶች ለልጅ ልጆቻቸው ህይውት በጣም ጠቃሚ ናቸው። ለልጅ ልጆች አያቶቻቸው ማለት ‘ከወላጆቻቸው ቤት ባሸገር ቤት የሚሰጣቸው’ ፤እና ደህንነት፤ ድጋፍ እና መጠን የሌለው ፍቅር የሚሰጧቸው ናቸው።

  • አያቶች የልጆች ወላጆች የማይኖራቸውን ብዙ ጊዜ ከልጅ ልጆቻቸው ጋር የሚያሰለፉት ሰዓት ይኖራቸዋል። ጊዜህን ከልጅ ልጆች በጠም በሚያዝናና መልኩ ለማጥፋት ሞክር ማለትም የልጆች መጨወቻ ስፍራ በመሄድ፤ ረጅም የእግር ጉዞ በማድረግና ለልጅ ልጆች ሰለዓለማቸው ማስተማር የመሳሰሉትን ማድረግ።
  • አያቶች ለልጅ ልጆቻቸው ጠቃሚ የሆነ ድጋፍ ሰጭ ናቸው። የልጅ ልጆችን ለማዳመጥ በቂ ጊዜ መስጠት ይገባል። የልጅ ልጆች በሚቸገሩበትና በሚጨነቁበት ጊዜ በመርዳት ችግራቸውን እነዲወጡት መርዳት ይቻላል።
  • ወላጆችና ልጆች በማይግባቡበት ጊዜ አያቶች አማራጭ ሃሳብ ሊሰጡ ይችላሉ ይህም ችግሮችን ለማቃለል ይረዳል። በዚህም ጊዜ ለማንኛቸውም ወገን ማድላት መሞከር አያስፈልግም ነገር ግን የልጅ ልጆችና ወላጆቻቸው እርስ በርሳቸው በተሻለ መንገድ እንዲግባቡ ለመረዳት ሞክር።
  • የልጅ ልጆች ሰለራሣቸው አለም ከአያቶቻቸው ጋር መወያየት ይችላሉ። የልጆ ልጆች ሰለ አዲሱ ቴክኖሎጂይ አያቶቻቸውን ማስተማር ይችላሉ በሌላ በኩል አያቶች ደግሞ አዲሱ ቴክኖሎጂ ከመምጣቱ በፊት እንዴት እንደሚሰራ እነደነበረና በቴክኖሎጂ ላይ ብቻ ሰለመተማናቸው ታሪኩን ለልጅ ልጆቻቸው ማካፈል ይችላሉ።
  • በልጅ ልጆች የተሳካ ውጤት አያቶች መደሰትና የልጅ ልጆቻቸውን ማሞገስ ይገባቸዋል። ይልጅ ልጆቻቸውን አዲሰ ነገሮችን እንዲሞክሩ ማበረታት ይገባል። ተስፋ ማድርግና ጥሩ ነገርን መመኘት እንዴት ጠሩ እንደሆን ማሳየት ይገባል።